Looking for more resources for supporting parents during COVID-19? Visit the Start Talking Now Facebook page.

ኮቪድ-19 የታዳጊዎችን የአዕምሮ ጤና እየጎዳ ነዉ። ወላጆች መርዳት ይችላሉ።

You are here

Home » ኮቪድ-19 የታዳጊዎችን የአዕምሮ ጤና እየጎዳ ነዉ። ወላጆች መርዳት ይችላሉ።

Read this page in English.

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአዕምሮ ጤናችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እያሳደረ ሲሆን ታዳጊዎች በተለይ ተጋላጭ ናቸው። አንጎላቸው ገና በማደግ ላይ በመሆኑ እና ገና ብዙ የሕይወት ልምዶች ስለሌሏቸው፣ የሚሰሟቸው ስሜቶች በሙሉ — ሀዘን፣ ንዴት፣ ጭንቀት እና መገለል— የበለጠ ከባድ ናቸው። እናም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት፣ ታዳጊዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ወይም የጭንቀት ምልክቶች የማሳየት ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ጥናት ያሳያል (Mental Health America)። ሴፕቴምበር 2020 ላይ፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ታዳጊዎች ራስን የማጥፋት ወይም ራስን የመጉዳት ሀሳቦች እንዳላቸው ሪፖርት አድርገዋል (Mental Health America)።

የምስራቹ ዜና ወላጆች እና ሌሎች የታመኑ አዋቂዎች መርዳት ይችላሉ

ምልክቶቹን ይወቁ

የመጀመሪያው እርምጃ ምልክቶቹን ማወቅ ነው። እያንዳንዱ ታዳጊ የተለየ ሲሆን ለትራውማቲክ (አሰቃቂ) ክስተቶች የሚሰጠው ምላሽ ይለያያል። "ወደ ውጭ ከማሳየት (acting out)" እስከ "በውስጥ አምቆ መያዝ (acting in)" ሊደርስ ይችላል። "ወደ ውጭ ማሳየት" እንደ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም፣ መደባደብ፣ ወይም የኮቪድ-19 የደህንነት መመሪያዎችን ችላ ማለት ያሉ አደጋዎችን መውሰድ ሊያካትት ይችላል። “በውስጥ አምቆ መያዝ” ልጅዎ ነገሮችን በመተው ስለማንኛውም ነገር ግድ የማይሰጠው ወይም ብዙ ጊዜ ብቻውን ለመሆን የሚፈልግ መስሎ እንዲታይ ሊያደርግ ይችላል (Washington State Department of Health)። በአደጋ ወቅት ሌሎች የተለመዱ የታዳጊዎች  ምላሾች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡

  • መጨነቅ
  • ሀዘን
  • የጥፋተኛነት ስሜት፣ ቁጣ፣ ፍርሃት፣ የመውደቅ ስሜት
  • ለእነሱ የወደፊት ተስፋ እንደሌለ መፍራት
  • ጓደኞችን አለማየት ወይም ጓደኞችን መለወጥ የመሳሰሉ በማህበራዊ ባህሪዎች ለውጦች
  • ስሜቶችን ለማስወገድ በሥራ መጠመድ
  • አልኮል ወይም አደንዛዥ ዕፅ አላግባብ መጠቀም

መርጃ መንገዶች

እንደ ወላጅ፣ በታዳጊ ልጆችዎ ሕይወት ውስጥ በጣም ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ነዎት። እነሱ አመኑም አላመኑም!

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ታዳጊዎች የበለጠ ብቸኝነት ሊሰማቸው ይችላል። በአካል የሚሰጥ ትምህርት፣ ጓደኞችን ማየት፣ ወይም ስፖርቶችን መጫወት በሌለበት፣ ቀደም ሲል ምናልባት ያገኙ የነበሩትን ተመሳሳይ ድጋፍ አይኖራቸውም። ለዚያም ነው ከታዳጊ ልጆችዎ ጋር ማውራት በጣም አስፈላጊ የሆነው። ከዚህ በታች ያሉት እርስዎ መርዳት የሚችሉባቸው መንገዶች ናቸው (Washington State Department of Health) ፡

  • የራስ-እንክብካቤን ሞዴል ያድርጉ እና በዚህ አደጋ መካከል ስለእራስዎ ስሜቶች ይናገሩ።
  • ታዳጊዎች ሀሳባቸውን እና ስሜታቸውን እንዲገልጹ ያበረታቷቸው። እነዚህን ስሜቶች እንዲለዩ እና እንዲቆጣጠሩ ይርዷቸው።
  • በዚህ ስሜት ብቻቸውን እንዳልሆኑ እና በዚህን ጊዜ እንደዚህ አይነት ስሜት መኖሩ የተለመደ መሆኑን ያስታውሷቸው።
  • ውጥረትን ለመቋቋም ራስን መንከባከብን እና ጤናማ መንገዶችን፣ ለምሳሌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ሜዲቴሽን፣ ከቤት መውጣት፣ ወይም የደስታ ወይም የሰላም ስሜትን የሚያመጣላቸውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንዲለማመዱ ያበረታቷቸው። ታዳጊዎች በ You Can ላይ ሀሳቦችን ማግኘት ይችላሉ።
  • ጤናማ ያልሆኑ የመቋቋሚያ መንገዶችን አደጋዎች (ትምህርታዊ ንግግር ሳይሰጡ) ይወያዩ፣ ለምሳሌ፡-
    • የአልኮል ወይም የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም
    • በአመጽ ወይም በሕገ -ወጥ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ
    • ጤናማ ባልሆኑ ግንኙነቶች ውስጥ መሆን
  • ጥሩ ውሳኔዎችን መወሰን ላይ የሚረዷቸውን ጓደኞች የመምረጥን አስፈላጊነት ተወያዩበት። ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ግንኙነት እንዲገነቡ ያበረታቱዋቸው።
  • በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሌሎችን እንዲረዱ ይፍቀዱላቸው እንዲሁም ያበረታቱዋቸው። ለምሳሌ፣ የአትክልት ቦታን ለመጀመር፣ ቆሻሻን ለማንሳት፣ ለትናንሽ ልጆች እንቅስቃሴዎችን ለማደራጀት መርዳት ወይም ጎረቤቶችን ሸቀጣሸቀጥ በመግዛት መርዳት ይችላሉ።
  • ከታዳጊዎች ጋር ስለ ወደ ፊታቸው ይነጋገሩ። ለምሳሌ፦ “በሚቀጥለው ዓመት ወይም በ 5 ዓመታት ውስጥ ምን ማድረግ ትፈልጋላችሁ?” ብለው ይጠይቁ። “ያንን ግብ ለመድረስ እንዲረዳችሁ አሁን ምን እያደረጋችሁ ሊሆን ይችላል?” “ወደዚያ ግብ የሚያደርሱዋችሁ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ላይ የምረዳችሁ ነገሮች አሉ?”
  • በዚህ በእውነት ወይም ፈታኝ ጨዋታ ከታዳጊ ልጆችዎ ጋር ውይይቱን አስደሳች እና አሳታፊ በሆነ መንገድ ይጀምሩ።

ድጋፍ ያግኙ

Teen Link: አንዳንድ ጊዜ ታዳጊ ልጆችዎ ከእኩዮቻቸው ጋር ለመነጋገር የበለጠ ምቾት ይሰማቸው ይሆናል። ያ ጥሩ ነው! በሠለጠኑ ታዳጊዎች የሚሠራው ምስጢሩ የተጠበቀ እና ነፃ የእገዛ መስመር ከ 6 እስከ 10 p.m PT (ፓሲፊክ ታይም)  አለ።  ልጆችዎ በአዕምሯቸው ውስጥ ስላለው ነገር ሁሉ ሊያነጋግሩዋቸው ይችላሉ። ልጆችዎ በ 1-866-TEENLINK (833-6546) ላይ እንዲደውሉ፣ እንዲጽፉ ወይም ቻት እንዲያደርጉ ያበረታቱዋቸው። ከፈለጉ፣ ልጆችዎ ከማድረጋቸው በፊት መጀመሪያ ከበጎ ፈቃደኛው ጋር መነጋገር ይችላሉ። ስለ ልጆችዎ  የአደንዛዥ እፆች ወይም አልኮል መጠቀም ስጋቶች ለመወያየትም የእገዛ መስመሩን ማነጋገር ይችላሉ።

Washington Listens: እርዳታ ለእርስዎም አለ። ስምዎ ሳይታወቅ በነጻ እርዳታ ለማግኘት በ 1-833-681-0211 ይደውሉ ወይም WAlistens.org ን ይጎበኙ። Washington Listens በኮቪድ-19 ምክንያት ሀዘን፣ የፍርሃት ጭንቀት ወይም ጭንቀት ለሚሰማቸው ድጋፍ ይሰጣል። የሚሠራው ከሰኞ-አርብ ከ 9 a.m. እስከ 9 p.m. PT እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድ ከ 9 a.m. እስከ 6 p.m. PT. ነው። TSR 711 እና የቋንቋ መዳረሻ አገልግሎቶች ይገኛሉ።

ያስታውሱ፣ እርዳታ መጠየቅ ጥሩ ነው። ታዳጊ ልጆችዎ እርስዎ ጭንቀትን እንዴት እንደሚቋቋሙ እየተመለከቱ ነው። ጤናማ የመቋቋሚያ መንገዶችን ማግኘት እና ድጋፍ በሚፈልጉበት ጊዜ መጠየቅ ለእርስዎ እና ለታዳጊ ልጆችዎ የሚማሩበት አዎንታዊ እርምጃዎች ናቸው።

ታዳጊ ልጆችዎን በደንብ ያውቃሉ እናም በዚህ ፈታኝ ጊዜ ውስጥ ሊረዷቸው ይችላሉ። በጋራ፣ ሁለታችሁም ጠንካራ ሆናችሁ መውጣት ትችላላችሁ። እናም ድጋፍ ከፈለጉ፣ ይጠይቁ!