Looking for more resources for supporting parents during COVID-19? Visit the Start Talking Now Facebook page.

ወላጆች እና አሳዳጊዎች

You are here

Home » ወላጆች እና አሳዳጊዎች

ሙሉ ጣቢያውን በአማርኛ ለመመልከት እዚህ ጠቅ ያድርጉ 

ይህ ገፅ በሚከተሉት ዙሪያ መረጃ ይዟል፦

ዕፆችን በሚመለከት የእርስዎ ታዳጊ ልጆች በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ትልቅ ኃላፊነት አለብዎት።

ከጓደኞች በላይ። ከታዋቂ ሰዎች በላይ። ለዚያም ነው ታዳጊዎች ማሪዋና፣ አልኮል ወይም ሌሎች ዕፆችን እንዳይጠቀሙ ከእርስዎ መስማት ያለባቸው እና በአስቸጋሪ ጊዜያትም ቢሆን ጤናማ አካሄዶችን ማወቅን ጨምሮ ጤናማ ውሳኔዎችን ለመወሰን ከእርስዎ መማር ያለባቸው።

ከታዳጊ ልጆችዎ ጋር በእነዚህ ርዕሶች ላይ ማውራት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት እርስዎ ለልጆቹ እንደሚያስቡ ለማሳየት፣ የሚጠበቅባቸውን ለማሳወቅ እና ደህንነታቸውና ጤናቸው ተጠብቆ እንዲቀጥሉ ለማገዝ ሊያከናውኗቸው ከሚገቡ በጣም ጠቃሚ ነገሮች ውስጥ አንዱ ይህ ጉዳይ ነው። ንግግሮቹ ቀለል ያሉ፣ ከታዳጊ ልጆችዎ ጋር ጊዜ ሲያሳልፉ በአጭሩ የሚያነሷቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ለእነዚህ ውይይቶች ዝግጅት ለማድረግ፣ ልጅዎ ስለ አልኮል እና ማሪዋና ሊያነሷቸው ለሚችሉ ጥያቄዎች መልሶች ዝርዝር እዚህ ቀርቦልዎታል። ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት አይደለም፣ ስለዚህ ምላሾችዎን ለራስዎ ዕይታዎች እና ተሞክሮዎች እንዲመቹ ማስተካከልዎን አይርሱ። ሰዋዊ እና ከልብ የሆነ ውይይት ማድረግ የበለጠ ከፍ ያለ ተፅዕኖ ይፈጥራል።

ከታዳጊ ልጆችዎ ጋር ለመነጋገር የሚያግዙ ተጨማሪ መረጃዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦

ጠቃሚ ምክሮች ለወላጆች እና ለአሳዳጊዎች።

ከታዳጊ ልጅዎ ጋር ጊዜ ያሳልፉ፣ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ያድርጉ እንዲሁም በጋራ አስደሳች ነገሮችን ያከናውኑ!

ግንኙነትዎን ሲያጠብቁ፣ ድንበሮችን ሲያስቀምጡ እና ክትትል ሲያደርጉ ልጅዎ ማሪዋና፣ አልኮል ወይም ሌሎች ዕፆችን እንዳይጠቀም/እንዳትጠቀም ማገዝ ይችላሉ።

ግንኙነቶችን ማጥበቅ።

ታዳጊ ልጆች ወላጆቻቸው እና/ወይም አሳዳጊዎቻቸው በህይወታቸው ተሳትፎ ሲኖራቸው እና ለእነርሱ ቅርብ እንደሆኑ ሲሰማቸው ማሪዋና ወይም ሌሎች ዕፆችን የመጠጣት ወይም የመጠቀም ዕድላቸው ይቀንሳል። የቤተሰብ ትስስርን ለመጨመር፦

  • በየዕለቱ ለልጅዎ ቢያንስ የ15 ደቂቃዎች የአንድ-ለአንድ ጊዜ ይስጡ።
  • መዝናኛ እንቅስቃሴዎችን በጋራ ይስሩ።
  • ልጅዎ በሚወስደው/በምትወስደው ጤናማ ውሳኔ ላይ አወንታዊ ግብረመልስ ይስጡ።
  • በጋራ ይመገቡ።

ግልፅ ድንበሮችን ያስቀምጡ።

ግልፅ ህጎችን አስቀድመው ያስቀምጡ፣ ወጥነት ያሳዩ እንዲሁም ስለ መመሪያዎች አዘውትረው ይናገሩ። ድንበሮችን ለማስቀመጥ፦

  • የሚጠብቋቸውን ጉዳዮች በሚመለከት መደበኛ ውይይት ያድርጉ።
  • ህጎችዎ በተጣሱ ጊዜ ፍትሃዊ የሆኑ እና ወጥነት ያላቸው ሂደቶችን ይተግብሩ።
  • ልጆችዎ ከጓደኞች ጋር አወንታዊ ግንኙነት እንዲመሰርቱ ያግዙ።
  • ልጅዎ ዕፅ መጠቀምን እምቢ የሚልባቸውን/የምትልባቸውን መንገዶች እንዲለማመድ/እንድትለማመድ ያግዙ።

መስተጋብሮችን ይከታተሉ።

ሁልጊዜም ቢሆን ልጅዎ ምን እና የት እንደሚሰራ/እንደምትሰራ እንዲሁም ከማን ጋር ጊዜ እንደሚያሳልፍ/እንደምታሳልፍ ይወቁ።  ለደህንነት ስጋት ያልሆኑ እና አስደሳች ተግባራትን እንዲያቅድ/እንድታቅድ ያግዙ። የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅዎን ያረጋግጡ፦

  • የት እየሄድክ/እየሄድሽ ነው?
  • ምን ለማድረግ?
  • ከማን ጋር ነው?
  • ወደ ቤት የምትመለሰው/የምትመለሽው ስንት ሰዓት ነው?
  • አልኮል፣ ማሪዋና ወይም ሌሎች ዕፆች ይኖራሉ?

እድሜያቸው ያልደረሰ ልጆች አልኮል፣ ማሪዋና እና ሌሎች ዕፆችን መውሰዳቸው የሚያሳድረው ሥጋት ምንድን ነው?

ቀደም ብለው አልኮል፣ ማሪዋና እና ሌሎች ዕፆችን የሚጀምሩ ታዳጊዎች በሱስ እና በሌሎች የጤና ችግሮች የመጠቃት፣ ከትምህርት ቤት የማቋረጥ እንዲሁም በእስራት እና በትምህርት ማነስ ምክንያት የሙያ ምርጫ ገደብ ሊገጥማቸው የመቻሉ ዕድል ከፍ ያለ ነው። ማሪዋና፣ አልኮል እና የሌላ ዕፅ መጠቀም፦

  • በእድገት ላይ በሚገኘው የታዳጊ አዕምሮ ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። አልኮል፣ ማሪዋና እና ሌሎች ዕፆችን የአዕምሮን የእንቅስቃሴ ማሳለጫ፣ የቅፅበታዊ ምላሽ መቆጣጠሪያ፣ የማስታወስ፣ የመማር እና ውሳኔ የማስተላለፊያ ክፍሎች ሊጎዱ ይችላሉ።  የታዳጊ ልጅ አዕምሮ እያደገ ያለ በመሆኑ፣ ለተፅዕኖዎች የበለጠ ተጋላጭ ነው።
  • ወደ ሱስ ሊያመራ ይችላል። ከ15 ዓመታቸው በፊት አልኮል መጠጣት የጀመሩ ልጆች ጎልማሳ ሲሆኑ የአልኮል ችግር የማዳበር ዕድላቸው አራት እጥፍ ሲሆን ከ18 ዓመት በፊት ማሪዋና መጠቀም የሚጀምሩት ደግሞ ዘግይተው ከሚጀምሩት ጋር ሲነፃጸሩ ከአራት እስከ ሰባት እጥፍ በማሪዋና መጠቀም የሚከሰት ምስቅልቅል ይገጥማቸዋል።
  • በታዳጊዎች ላይ ሞት ከሚያስከትሉ ሦስት ቀዳሚ ምክንያቶች መካከል ነው፦ አደጋዎች (የትራፊክ እና የመስመጥ አደጋዎችን ጨምሮ)፣ በሰው መገደል እና ራስን ማጥፋት።

ዕድሜያቸው ያልደረሱ ልጆች የዕፅ መጠቀምን በሚመለከት ዕውነታዎችን ያግኙ

በጋራ ጤናማ ባህሪያትን ማዳበር።

ታዳጊ ልጆችዎ ጤናማ ልምዶችን እንዲያዳብሩ፣ ግቦችን እንዲያስቀምጡ እና ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ጤናማ መንገዶችን እንዲለማመዱ ያግዟቸው።

  • ግቦችን ማስቀመጥ፦ ግቦችን ማስቀመጥ ሰዎች ዓላማ እንዲኖራቸው እና ወደፊት አወንታዊ ነገሮችን እንዲጠብቁ ያግዛቸዋል። አሁን ፈታኝ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፣ የወደፊት ዕድሎችን በሚመለከት ጥሩ ተስፋ ካለ ለመቋቋም ቀላል ነው። ታዳጊ ልጅዎ ወደፊት ማድረግ ስለሚፈልገው/ስለምትፈልገው ነገር ይነጋገሩ እና ዕቅዶችን እድኒያወጣ/እንድታወጣ ድጋፍ ያድርጉ።
  • ጤናማ ባህሪያትን መገንባት፦ በደንብ መመገብ እንዲሁም በቂ እንቅልፍ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የጤናን እና የስሜትን ሁኔታ ያስተካክላል። መልካም የአመጋገብ ልምዶች እንዲኖሩ ቅርፅ ያስይዙ (ለምሳሌ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት)፣ እንዲሁም ጤናማ ባህሪያት ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ ለልጅዎ ያስረዱ። በጋራ፣ ጥሩ የአመጋገብ ልምድ የሚያጠነክሩባቸውን ስልቶች ይንደፉ።
  • የመቋቋም ክህሎቶችን ያዳብሩ፦ ታዳጊ ልጆች የመጨነቅ ወይም የመረበሽ ስሜት ሲሰማቸው የተሻለ ስሜት እንዲኖራቸው የሚያደርጉባቸውን እቅንስቃሴዎች መለየት መቻላቸው አስፈላጊ ነው። ከታዳጊ ልጅዎ ጋር፣ እነዚያን እንቅስቃሴዎች የህይወቱ/ቷ አካል የሚያደርግበትን/የምታደርግበትን መንገድ ይፈልጉ — ከራት በኋላ ኳስ በግቢ ውስጥ መወርወር፣ የእግር ጉዞ ሰፈርውስጥ ማድረግ፣ ዕለታዊ የጥበብ ጊዜ ሰዓት ወይም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሲሆኑ እስከ 10 መቁጠርና በደንብ መተንፈስ ሊሆን ይችላል።

ድጋፍ ያግኙ።

ለእርስዎ እና ለታዳጊዎ እገዛን መጠየቅም ችግር የለውም! ከታች ያሉት መገልገያዎች በሙሉ የቴሌኮምንኬሽን ሪሌይ አገልግሎት TSR 711 እና የቋንቋ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።

  • Teen Link ነፃ፣ በሚስጥር የሚደረግ፣ ታዳጊዎች በመደወል፣ በፅሁፍ ወይም በጽሁፍ ምልልስ ስልጠና ከወሰዱ ታዳጊዎች ጋር ከ 6 እስከ 10 p.m. ፓስፊክ ታይም ጋር ለመገናኘት መዳረሻ የሚያገኙበት የእገዛ መስመር ነው። ልጅዎ በአዕምሮው/ዋ ውስጥ የሚገኘውን ማንኝውም ነገር ማውራት ይችላል/ትችላለች። ልጅዎ 1-866-TEENLINK (833-6546) ላይ በመደወል፣ በፅሁፍ ወይም በፅሁፍ ምልልስ እንዲያነጋግሩ ያበረታቷቸው። በተጨማሪም ጎልማሶች ወደ Teen Link በመደወል የዕፅ መጠቀምን ስለመከላከል ልዩ ሙያ ካላቸው ባለሙያ ጋር መነጋገር ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ www.teenlink.org ይጎብኙ።
  • Washington Recovery Help Line በዕፅ መጠቀም ቀውስ እና በአዕምሮ ህመም ተግዳሮቶች ችግር የሚገጥማቸውን ሰዎች ማንነትን ሳይገልፅ በሚስጥራዊነት የ24-ሰዓት እገዛ የሚያቀርብ መስመር ነው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 1-866-789-1511 ላይ ይደውሉ ወይም WARecoveryHelpLine.org ይጎብኙ።
  • Washington Listens ሀዘን፣ መረበሽ ወይም መጨነቅ ለሚሰማቸው ሰዎች እገዛ ያቀርባል። ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ9 ኤ.ኤም እስከ 9 ፒ.ኤም ፓስፊክ ታይም እና ቅዳሜና እሁድ ከ 9 a.m. እስከ 6 p.m. ፓስፊክ ታይም ሰራተኞች ይኖራሉ። ለተጨማሪ መረጃ Washington Listens ይጎብኙ።